በመዲናዋ ለከተማየ ውበት እኔም አምባሳደር ነኝ” በሚል ንቅናቄ ከ25 ሺህ በላይ ወጣቶችን በማሳተፍ እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባን ጽዱና ውብ ከተማ ለማድረግ “ለከተማየ ውበት እኔም አምባሳደር ነኝ” በሚል ንቅናቄ ከ25 ሺህ በላይ ወጣቶችን በማሳተፍ አካባቢን የማጽዳት ስራ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ ገለጸ።
ለሁለት ወር የሚቆየው የጽዳት ንቅናቄ አርቲስቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የስፖርት ማህበረሰቡ እና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተሳታፊ የሚሆንበት ነው ተብሏል።
መንግስት ደረቅ ቆሻሻን ለማሰባሰብ እና ለማስወገድ በዓመት ግማሽ ሚሊየን ብር ወጪ እንደሚያደርግ የኢቢሲ ዘገባ ያመላክታል።
ይህንኑ ደረቅ ቆሻሻ ወደ ተለያዩ ምርቶች ለመቀየር እየሰራ መሆኑንም ኤጀንሲው ገልጿል።
ጽዱና ውብ ከተማን ለመፍጠር ሁሉም ህብረተሰብ ቆሻሻን በባለቤትነት ሊያጸዳ እንደሚገባ በዚህ ወቅት ተገልጿል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!