Fana: At a Speed of Life!

በቤልጅየም የኢፌዴሪ ኤምባሲ፥ በቤኔሉክስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅ/ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በበይነ መረብ የቱሪዝም ማስተዋወቅ አካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልጅየም የኢትዮጵያ ኤምባሲና በቤኔሉክስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በጋራ በመሆን የኢትዮጵያ ቱሪዝም ዕድሎችን በማስተዋወቅ ላይ ውይይት አካሂደዋል።

ውይይቱ ኢትዮጵያ ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን የሚያስችል የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ነው ተብሏል።

የመድረኩ ዓላማ የቤልጅየምና ሉክዘምበርግ አስጎብኝ ድርጅቶችን ከኢትዮጵያ አስጎብኝ ድርጅቶች ጋር በማቀራረብ በሁለቱ ሃገራት የጎብኚዎችን ቁጥር ለመጨመር ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

መድረኩን አምባሳደር ሂሩት ዘመነ የመሩ ሲሆን በኢትዮጵያ የቤልጅየም አምባሰደር ፍራንስዋ ዱሞንትም ተሳትፈዋል፡፡

የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ስለሽ ግርማ ፣የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤሪያል ማናጄር ፣የኢትዮጵያ ሆቴሎች ማህበር ተወካዮች ፣የኢትዮጵያ ቱር ኦፕሬተሮች ማህበር ተወካዮች፣የሁለቱም ወገኖች የጉዞ ወኪሎች ውይይቱን ተካፍለዋል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዕድሎችን በተመለከተ የተለያዩ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በቤልጅየም የኢፌዴሪ ኤምባሲ፥ በቤኔሉክስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅ/ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በበይነ መረብ የቱሪዝም ማስተዋወቅ አካሄደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.