Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው የኮቪድ-19 ክትባትን ለመቀበል አና ለማሰራጨት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የኮቪድ-19 ክትባትን ለመቀበል አና በመላ ኢትዮጵያ ለማሰራጨት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለጸ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ እንዳስታወቁት ኤጀንሲው በአሁኑ ሰዓት 100 ሜትር ኩዩብ የሚይዘውን ተጨማሪ የቀዝቃዛ ሰንሰለት ዝግጅት ሙሉ በሙሉ አጠናቋል።

300 ሜትር ኪዩብ የሚይዝ የማቀዝቀዣ ተጨማሪ ክፍል ዝግጅትም በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው የሙቀት መጠናቸው ከ 2-8 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ማቀዝቀዝ እንደሚችል ገልጸዋል።

ኤጀንሲው ከአሁን በፊት በዋና መስሪያ ቤቱ የቀዝቃዛ ሰንሰለት 1940 ሜትር ኪዩብ የቀዝቃዛ ክፍሎች ፤ ከ 2 እስከ 8 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ቅዝቃዜ ለሚያስፈልጋቸው መድሓኒቶች የሚያገለግሉ ሲሆን በተጨማሪም 1 የከፍተኛ ቀዝቃዛ ክፍል 100 ሜ ኩዩብ የመያዝ አቅም ያለዉ ከ -25 እስከ -15 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ቅዝቃዜ ለሚያስፈልጋቸው የህክምና ግብዓቶች ለማከማቸት የሚቻስችሉ ናቸው ብለዋል።

በአጠቃላይ መጋዘኑ 2 ሺህ 40 ኩዩቢክ ሜትር የመያዝ አቅም ያለው መሆኑ ገልጸዋል።

ለ ኮቪድ 19 ክትባት ተብለዉ የተገነቡ አዲስ ማቀዝቀዣዎች ከ -25 እስከ -15 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የማከማቸት አቅምን ከ 100 ሜትር ኪዩብ ወደ 200 ሜትር ኪዩብ ያሳደገ ሲሆን ከ 2 እስከ 8 ድግሪ ሴንቲግሬድ የማከማቸት አቅምን ደግሞ ከ 1940 ሜትር ኪዩብ ወደ 2240 ሜትር ኪዩብ አሳድጓል።

በአሁኑ ወቅት በመገጠም ለይ ያሉትን ጨምሮ በአንድ አመት ጊዜ 1400 ሜትር ኪዩብ የቅዝቃዜ መጋዘን ተገንብቷል።

በአጠቃላይ ኤጄንሲው 4607 ሜትር ኪዩብ የቅዝቃዜ መጋዘን እንዳለው ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ከዚህ ዉስጥ 2167 ሜትር ኪዩብ በቅርንጫፎች ያለ ሲሆን ቀሪው 2440 ሜትር ኪዩብ በዋና መስሪያ ቤት ያለ ነዉ ።

በተጨማሪም 17 ማቀዝቀዣ የተገጠመላቸው ተሽከርካሪዎች ክትባቱን በመላ ሀገሪቱ ለማሠራጨት ዝግጁ ሆነው በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ ነው ያሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.