Fana: At a Speed of Life!

በደብረ ማርቆስ ከተማ አዲስ በሚገነባው የአውሮፕላን ማረፊያ እና የባህር ዳር ኤርፖርት ተርሚናል እድሳት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡
ውይይቱ የደብረ ማርቆስ አየር ማረፊያ ግንባታን ለመጀመር በሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን በዚህ ረገድ ለሚገነባው ኤርፖርት ልማት የሚያስፈልገውን የወሰን ማስከበር ስራ የአማራ ክልል ከሶስተኛ ወገን አጥርቶ እንዲያስረክብ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
በመሆኑም የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት የጀመረውን ጥናትና ዲዛይን በማጠናቀቅ በቀጣይነት ለሚካሄደው ግንባታ አስፈላጊው የጨረታ ሂደት እንዲካሄድ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡
በተጨማሪም በህግ ማስከበር ዘመቻው ጉዳት የደረሰበትን የባህር ዳር የአውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ እንዲመለስ በአስቸኳይ እድሳት እንዲደረግለት ተወስኗል፡፡
ለዚህም የሚያስፈልገው ወጪን የፌዴራል መንግሰት እንደሚሸፍን በውይይቱ ላይ መጠቀሱን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.