Fana: At a Speed of Life!

በሩዝ ልማት የተመዘገበውን አስደናቂ ለውጥ ለማስቀል በቅንጅት መስራት ይገባል – ሚኒስቴሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሩዝ ልማት የተመዘገበውን አስደናቂ ለውጥ ለማስቀል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰራ ይገባል አለ የግብር ሚኒስቴር፡፡

ሚኒስቴሩ የሩዝ ልማት በብሔራዊ ፍላግሺፕ ፕሮግራም ደረጃ ከተያዘ ጀምሮ ያለውን የሁለት ዓመት ተኩል የሩዝ ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት አካሂዷል፡፡

በሚኒስቴሩ የእርሻ እና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ደሳለኝ ተሻለ በዚህ ወቅት ÷ ሩዝ በ10 ዓመቱ የግብርና መሪ ዕቅድ በትኩረት ሊሰራባቸው ከተለዩ የግብርና ምርቶች አንዱ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በሩዝ ልማት ላይ በትኩረት በመሰራቱ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ነው አጽንኦት የሰጡት፡፡

ለአብነትም በአነስተኛ አርሶ አደር በመኸር ሩዝ በ2012 ዓ.ም ይለማ ከነበረው 60 ሺህ ሄክታር መሬት በ2017 ዓ.ም ወደ 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር ማሳደግ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

እንዲሁም በ2012 ዓ.ም ከነበረበት 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል ምርት በ2017 ዓ.ም ወደ 62 ነጥብ 9 ሚሊየን ኩንታል ማሳደግ እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡

ከውጭ የሚገባው የሩዝ ምርት በ2012 ዓ.ም ከነበረበት 13 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል በ2017 ወደ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እንደቀነሰና በዚህም 442 ሚሊየን ዶላር ማዳን መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

በሩዝ ልማት የተመዘገበውን አስደናቂ ለውጥ አጠናክሮ ለማስቀል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት በመስራት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ማሳሰባቸውን ሚኒስቴሩ ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል።

በመድረኩ በሩዝ ልማት የተገኙ ስኬቶች እንዲሁም ወደፊት በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መቀረፍ የሚገባቸው ተግዳሮቶች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.