የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔና የቋሚ ኮሚቴ አባላት የጎተራ-ቄራ-ሳር ቤት መንገድን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔን ጨምሮ የቋሚ ኮሚቴ አባላት የጎተራ – ቄራ – ሳር ቤት መንገድ ግንባታን ጎብኝተዋል።
የፑሽኪን ወይንም ሳር ቤት አደባባይ – ቄራ – ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት 3.8 ኪ.ሜ ርዝመት እና ከ30 እስከ 45 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ነው።
ይህ ፕሮጀክት በመዲናዋ በቢሊዮን ብር ወጪ ከሚደረግባቸው ግዙፍ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንደኛው ነው።
ግንባታውንም ቻይና ፈርስት ሀይዌይ ኢንጂነሪንግ በ1.5 ቢሊዮን ብር ዋጋ በሁለት ዓመት ተኩል ለማከናወን ውል ገብቷል።
የመንገድ ፕሮጀክቱ 320 ሜትር የሚረዝም ዋሻ እና ሁለት ትላልቅ ማሳለጫዎች ያሉት በመሆኑ የመዲናዋን ገጽታ የሚያሻሽል እና ተጨማሪ ውበት የሚፈጥር ነው።
መንገዱ ከቂርቆስ፣ ጎተራ፣ ሳርቤት፣ ሜክሲኮ፣ ቄራ እና ጎፋ የሚመጡ ተሽከርካሪዎችን በአግባቡ ማስተናገድ የሚችል አቅም ያለው ነው።
መንገዱ ከፑሽኪን እና ጎተራ ማሳለጫዎች ጋር በመመጋገብ በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ማስቀረት የሚያስችል ትልቅ ፕሮጀክት መሆኑን ኢቢሲ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን