Fana: At a Speed of Life!

በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ውይይት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ዓለም አቀፍ ህግ፣ የግጭት አፈታትና ሉዓላዊነት በሚሉ ጉዳዮች በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ውይይት እየተደረገ ነው።
የመድረኩ ዓላማ ምክንያታዊ ያልሆነውን ጫና በመረዳት ጫናውን በተጠና እና ምክንታዊ በሆነ መንገድ መመለስ መሆኑን የሳይንስ እና ከፍተኛ ሚኒስትር ዲኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ተናግረዋል።
ውይይቱ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ ዘጠነኛው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉባኤ ነው ተብሏል።
በመድረኩ በግድብ ዙሪያ ጥናት ያደረጉ ምሁራንና አምባሳደሮች ተገኝተዋል፡፡
ውይይቱ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በመጀመሪያው ቀን በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በመምከር በሁለተኛው ቀን በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሚቀጥል ይሆናል።
በክብረወሰን ኑሩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.