የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 100 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት ከጎጆ ብሪጅ ማህበር ጋር ተስማማ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመዲናዋ 100 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት ከጎጆ ብሪጅ ማህበር ጋር የውል ስምምነት ተፈራርሟል።
የከተማ አስተዳደሩ የመኖሪያ ቤት ችግርን ከማቅለል አንፃር የተያዘውን እቅድ ለመተግበር ሲባል አብሮ ለመስራት መስማማቱ ተገልጿል።
ይህ ማህበር በቅርቡ ከ1 ሺህ የሚልቁና ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶችን ለመገንባት የዲዛይን ስራ እያከናወነ መሆኑን የኢቢሲ ዘገባ ያመላክታል።
በቀጣይም በዋነኛነት መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ግለሰቦች የጋራ መኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ማድረግ ላይ በማተኮር ቤት ተመዝግበው ለሚጠባበቁ እንዲሁም በማህበር ተደራጅተው እየተጠባበቁ ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችን ለመደገፍ ማለሙ ተገልጿል።
የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ አልማው ጋሪ ማህበሩ ቤቶችን በእቅዱ መሰረት ሰርቶ ለማስረከብ እና ሀላፊነቱን ለመወጣት እንደሚንቀሳቀስ ገልጸዋል።
ጎጆ ብሪጅ የግል ይዞታ ኖሯቸው መገንባት ያልቻሉ ግለሰቦችን በማህበር በማደራጀት ከቦታቸው ሳይነሱ ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት በማለም ከሶስት ዓመታት በፊት የተደራጀ ማህበር ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!