Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም የአድቫንስድ 4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት በደቡብ ምዕራብ ሪጅን አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣2013(ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮ ቴሌኮም የአድቫንስድ 4ጂ ኤል.ቲ.ኤል አገልግሎት በደቡብ ምዕራብ ሪጅን አስጀምሯል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም  በአገልግሎቱ ጅማ፣ አጋሮ፣ በደሌ፣ ቦንጋ፣ ኮይሻ፣ መቱ፣ ማሻ ፣ ሚዛንና ቴፒ ከተሞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጿል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ምዕራብ ሪጅን የሚሰጠዉን የኤል.ቲ.ኢ ዘመናዊ አገልግሎት በጅማ ከተማ የምረቃ መርሃ ግብር አስጀምሯል፡፡

በምረቃ መርሃ ግብሩ የኢትዮ ቴሌኮም ስራ አስፈጻሚ ቴሌብርን በተመለከተ ለተሳታፊዎች ገለፃ ያደረጉ ሲሆን፥ ህብረተሰቡ ቴሌብርን በመጠቀም የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴውን እንዲያቀል ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ በጅማ ከተማ በተካሄደው የአገልግሎቱ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ እንደተናገሩት በጅማ ከተማ እና በአካባቢው በተደረገው የኔትዎርክ ማስፋፊያ በአሁኑ ወቅት ከ350 ሺህ በላይ ደንበኞችን የኤል ቲ ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

በተጨማሪም ኩባንያው በተያዘው በጀት አመት 103 ከተሞችን የአራተኛ ትውልድ (4 ጂ) ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ እስካሁን በመላው ኢትዮጵያ 52 ከተሞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

በቀጣይም ኩባንያው በተመሳሳይ ሁኔታ የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሠረት ባደረገ መልኩ በዕቅድ ይዞ እያከናወናቸው ያሉ የአራተኛ ትውልድ (4ጂ) ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት የማስፋፊያ ሥራዎችን በማጠናቀቅ በተለያዩ የክልል ከተሞች አገልግሎቱን በቅርቡ ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

በማህሌት ተክለብርሃን እና ሙክታር ጠሃ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.