በጋሞ ዞን 6ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የጋሞ ዞን ምርጫ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ገለፀ ።
የማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አብራሃም አንጅሎ፥ በዞኑ ባሉት 10 ምርጫ ክልሎች ላይ 599ሺህ 964 ስው ድምጽ ለመስጠት ተመዝግቧል ።
በ810 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ 10 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች እንደሚወዳደሩ የገለጹት ኃላፊው 175 ለክልል እና 65 ለህዝብ ተወካዮች በዕጩነት ተመዝግበዋል ።
ድምጽ ለመስጠት የሚያገለግሉ የቁሳቁስ ስርጭትም መደረጉን ተናግረዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ሰላምና ፀጥታን ለማስከበር የተለያዩ ባላድርሻ አካላትን በማቀናጀት እየተሰራ መሆኑን የገለፁጽ ደግሞ የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ደግፌ ደበላ ናቸዉ።
ምርጫዉ በሁለንተናዊ መልኩ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከፖሊስ፣ፀጥታ፣ሚልሻ፤ ከዐቃቤ እና ከለሎቹ ባላድርሻ አካላት ጋር በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል ።
በማቴዎስ ፈለቀ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!