Fana: At a Speed of Life!

የከተማዋን ነዋሪዎች የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ ተጨባጭ ስራዎች ተከናውነዋል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ስድስት ወራት የከተማዋን ነዋሪዎች የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ ተጨባጭ ስራዎች ተከናውነዋል አሉ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባለፉት 6 ወራት በንግዱ ዘርፍ የተከናወኑ ስራዎችን በተመለከተ ለምክር ቤቱ አባላት ባቀረቡት ሪፖርት የገበያ መረጋጋት እና የምርት አቅርቦትን ለማሳደግ በትኩረት መሰራቱን ተናግረዋል።

በዚህም 688 ሺህ 153 ኩንታል በላይ ሰብል፣ 2 ሚሊየን 127 ሺህ 208 በላይ ዳልጋ ክብት እና በግና ፍየል እንዲሁም 3 ሚሊየን 899 ሺህ 375 ኩንታል በላይ አትክልትና ፍራፍሬ ለገበያ ማቅረብ መቻሉን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም 12 ሚሊየን 601 ሺህ 755 ሊትር የምግብ ዘይትና 242 ሺህ 892 ኩንታል ስኳር በማቅረብ የከተማዋን ነዋሪዎች የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ ተጨባጭ ስራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል፡፡

የንግድ መሠረተ ልማት እና ቁጥጥርን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ የደላላን ሰንሰለት ለመበጠስና ሸማቹን ከአምራች ጋር በቀጥታ ለማገናኘት ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን አመልክተዋል።

በአምስቱ የከተማ መግቢያዎች ከተገነቡት በተጨማሪ የላፍቶ ቁጥር 2 ገበያ ማዕከል ወደ አገልግሎት መግባቱን ጠቅሰው÷ የቅዳሜና እሁድ የገበያ ቦታዎች ቁጥርን ከ219 ወደ 245 ከፍ እንዲል መደረጉን ገልጸዋል።

በ230 ሺህ 13 ድርጅቶች ላይ ክትትል በማድረግ 12 ሺህ 139 ጥፋተኞች መለየታቸውንና ከእነዚህም ውስጥ 10 ሺህ 496 ነጋዴዎች ወደ ህጋዊ መስመር መመለሳቸውን ጠቅሰዋል።

7 ሺህ 400 መደበኛ ያልሆኑ አነስተኛ ንግዶችን ህጋዊ እውቅና በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓልም ነው ያሉት ከንቲባዋ በሪፖርታቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.