Fana: At a Speed of Life!

በህንድ በኮሮና ምክንያት የሟቾች ቁጥር ከ400 ሺህ አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ በኮሮና ምክንያት ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 400 ሺህ ተሻግሯል፡፡
በሃገሪቱ በቫይረሱ ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ሲሆን ባለፉት 39 ቀናት ብቻ የ100 ሺህ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡
ከሟቾቹ መካከል ግማሾቹ ባለፉት ጥቂት ወራት በሁለተኛው የኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡
ህንድ ወረርሽኙ ከተከሰተ ወዲህ 30 ነጥብ 4 ሚሊየን ዜጎቿ ቫይረሱ ሲገኝባቸው፥ በአሜሪከ ደግሞ ከ33 ሚሊየን በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.