የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው በኢትዮጵያ የሃንጋሪ አምባሳደር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ሰኔ 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው በኢትዮጵያ የሃንጋሪ አምባሳደር ከሆኑት አቲላ ኮፓኒ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸው በሁለቱ ሃገራት ሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
በምክክራቸው አምባሳደሩ በቡዳፔስት ከተማ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከመስከረም ወር ጀምሮ በሚካሄደው የሃንጋሪ ቱሪዝም ንግድ ትርዒት ላይ ኢትዮጵያ እንድትሳተፍ ጋበዘዋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪዝም መስህቦች ለማስተዋወቅ መልካም ዕድል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ የጣሊያን ባህል ኢንቲትዩትም የሃንጋሪ የሙዚቃ ቡድን ባዘጋጀው የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ በክብር እንግድነት እንዲገኙ ሚንስትሯን መጋበዛቸውን ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በአቅም ግንባታ ዙሪያም የውጭ የትምህርት ዕድል በባህል፣ በቱሪዝምና በስፖርት መስክ እንዲመቻች ፍላጎት እንዳላቸው በጋራ ውይይቱ ከተነሱ ጉዳዮች ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን