Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ የክረምት በጎ አድራጎት መርሃ-ግብርን ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ የክረምት በጎ አድራጎት መርሃ-ግብር በይፋ ጀምሯል፡፡

የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮች በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የአቅመ ደካሞችን ቤቶች በማደስ ነው በትምህርት ዘርፉ የሚካሄደውን የክረምት የበጎ አድራጎት መርሃ-ግብር ያስጀመሩት፡፡

በበጎ አድራጎት መርሃ ግብሩም በትምህርት ሚኒስቴር ድጋፍ በክፍለ ከተማው 15 የአቅመ ደካሞች ቤት የሚታደስ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የሆነው የመተጋገዝ እና የመደጋገፍ ባህልን መሰረት በማድረግ የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ በመቻላችን ደስታ ይሰማናል ብለዋል።

በሁለት ሳምንት ውስጥም ቤቶቹ ታድሰው ለነዋሪዎቹ እንደሚያስረክቡም ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።

ለአቅመ ደካሞቹም ቤቱን ከማደስ ባሻገር አስፈላጊ የቤት እቃዎችም እንደሚሟሉላቸውም ከሚኒስቴ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ተማሪዎች በክረምቱ መርሃ-ግብር በየአካባቢያቸው በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች በመሳተፍ ከወገን አልፈው ሀገርን የማገዝ ሃላፊነታቸውን በንቃት እንዲወጡም ጥሪ ቀርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.