ጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባሄውን ዛሬ ማካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡
ጨፌው በ14 መደበኛ፣ 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ 6ኛ ዓመት ጉባኤው የ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ተጨማሪ በጀት ማጽደቅን ጨምሮ 11 አጀንዳዎች ላይ ይወያያል።
በ2013 በጀት ዓመት በአብዛኛው ለካፒታል ስራ የዋለ የ14 ቢሊየን ብር ተጨማሪ ረቂቅ በጀት ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ጉባሄው በአዳማ ከተማ በገልማ አባ ገዳ አዳራሽ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
ጨፌው በዛሬው ጉባኤው በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ከማዕረጋቸው በተጨማሪ “ጀግና” ተብለው እንዲጠሩና ማንኛውንም አገልግሎት ሲፈልጉ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ወስኗል።
በዳግማዊ ዴክሲሳ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!