Fana: At a Speed of Life!

ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

ከመዲናዋ ሁሉም ክፍለ ከተሞች የተወከሉ የህብረተሰብ ክፍሎችና የሀይማኖት አባቶች ጋር በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ መለስ አለም አቶ መለሰ እንደተናገሩት ከቁሳቁስና እናቶች ከሚያዘጋጁት የሰራዊት ስንቅ በተጨማሪ ህዝቡን በማስተባበር የ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ለመከላከያ ሰራዊት የገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን በአንድነት በመቆም ሃገርን ለማፍረስ በውስጥም በውጭም የተሰለፉ ሀይሎችን እያሳፈርን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

ህዝቡም በገንዘብ፣ በቁሳቁስ እንዲሁም በሰው ሀይል ደጀንነቱን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት በበኩላቸው፥ መከላከያ ሰራዊት ከሃገሩ አልፎ ለሌሎችም አለኝታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሰራዊቱ ከተበተነበት የተሰበሰበን የጁንታ ቅሪት ለመደቆስ የሚሰጠውን ትዕዛዝ እንደሚጠባበቅ አስረድተዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎችም ለሃገርና ለህዝብ መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት ደጀን ከመሆን በተጨማሩ ከጎኑ ለመሰለፍም ዝግጁ እንደሆኑ መግለጻቸውን የብልፅግና ፓርቲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.