Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ አሸንፋለች ሰላሟንም ትጠብቃለች-የአዲስ አበባ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሃት ጁንታን የሚቃወምና የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል፡፡
በሰልፉ ነዋሪዎቹ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ ሲሆን ÷ ከእነዚህ ውስጥ በህወሃት ጁንታ ስንደማ አንኖርም፣ የውስጣዊ አንድነታችንን በማጠናከር የውጭ ጣልቃ ገብነትን እንመክታለን፣ ክብር ለሃገር ሲሉ መስዋዕትነትል ለከፈሉ የጀግናው ሰራዊታችን አባላት፣ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚወራረድ ሂሳብ የለም፣ ኢትዮጵያን መነጣጠል አይቻልም፡፡
እንዲሁም የትግራይ ህዝብ አካላችን አሸባሪው ጁንታ ጠላታችን፣ መከላከያ ሰራዊታችን የሉዓዓላዊነታችን ምልክት ነው፣ ኢትዮጵያ አሸንፋለች ሰላሟንም ትጠብቃለች፣ ክረምቶች ቤት ፈርሰው የሚታደሱበት እንጂ ኢትዮጵያ የምትፈርስበት አይደለም የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን አሰምተዋል፡፡

በአብርሃም ፈቀደና በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.