Fana: At a Speed of Life!

የበደር የትራንስፖርት ማህበር አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ሃምሌ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመው የበደር የትራንስፖርት ማህበር አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ዛሬ ተካሂዷል።
በክልሉ ተወላጆች የተቋቋመው የበደር ትራንስፖርት አገልግሎት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ መሀመድ ዩሱፍ፣ የክልሉ መንገድ ትራንስፖርት ምክትል ሀላፊ አቶ መሀመድ አብዱረህማን እንዲሁም የተለያዩ የክልሉ የስራ ሃላፊውችና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት ተጀምሯል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ መሀመድ ዩሱፍ÷ የበደር ትራንስፖርት ማህበር በክልሉ የተለያዩ አቅጣጫዎች የመንገድ ስራዎች እየተተገበሩ ስለሚገኙ የትራንስፖርት ተደራሽነትን ለማስፋት እንደሚያስችለው ገልፀዋል፡፡
የበደር ትራንስፖርት እየተስፋፋ የመጣውን አደጋ ለመቀነስ የፍጥነት መገደቢያ (ስፒድ ሊሚት) የተገጠመለት፣ የኢንተርኔት ያለውና ለትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎቹ ምቹ ሆኖ እንዲያገለግል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር መሃሙድ መሃመድ መናገራቸውን የሶማሌ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡
የበደር ማህበር በከተማ ትራንስፖርትና በመካከለኛ ሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት ዘርፍ የሚሰማራ ሲሆን÷ በቅድሚያም አገልግሎቶቹን በጅግጅጋ፣ ቱጉጫሌ፣ ደገሀቡርና ድሬዳዋ ከተሞች እንደሚጀምር ተመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.