ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር በሙኒክ ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር በሙኒክ ተካሄደ።
በጀርመን-ሙኒክ በኢትዮጵያ ማህበረሰብ አዘጋጅነት በተዘጋጀው በዚህ ፕሮግራም ላይ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል።
በተለያዩ ዘርፎች ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር”ደግሞ ለዓባይ!” በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል።
በፕሮግራሙ ላይ ኢትዮጵያውያኑ እና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ በቦንድ ግዥ፣ በመጽሔት ሽያጭና በስጦታ “ደግሞ ለዓባይ” በማለት በከፍተኛ ቁጭትና ፍላጎት የተሳተፉ ሲሆን በዚህም ከ15 ሺህ ዩሮ በላይ ገቢ ማሰባሰብ ተችሏል።
በጀርመን – ፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል ጽህፈት ቤት ቆንስል ጄኔራል አቶ ፈቃዱ በየነ በወቅቱ ባስተላለፉት መልእክት÷ በሚወዷት ሀገራቸው ሥም ተሰብስበው ሕዳሴ ግድቡን ለመደገፍ በመገኘታቸው ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
በጀርመን ሙኒክ አካባቢ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በሁሉም ዘርፍ ሀገራቸውን ሲደግፉ የነበሩ መሆናቸውን በማውሳት÷ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቦንድ የተለመደ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉና በቀጣይነት ይህንን ስብስብ ወደ መላው የኢትዮጵያ ቀን በማሳደግ በአንድነት ከሀገራቸው ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።
በጀርመን ሙኒክ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የቦንድ ግዢውን ሲፈጽሙ እንደተናገሩት÷ በዚህ ታሪካዊ ቀንም የዜግነታቸውን ድርሻ ለመወጣት ሀገራቸውን ለመደገፍ በመገኘታቸው የዜግነት ክብር እንደሚሰማቸው በመግለጽ በሁሉም ዘርፍ ድጋፋችንን አጠናክረን በማስቀጠል ለሀገራችን ያለንን ፍቅር በተግባር እንገልጻለን ማለታቸውንከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!




+2
0
People Reached
315
Engagements
Boost Post
303
4 Comments
8 Shares
Like
Comment
Share