Fana: At a Speed of Life!

ህፃናትን ለጦርነት የሚያሰማራው አሸባሪው ቡድን በጦር ወንጀል እንዲጠየቅ ስራዎች መጀመር አለባቸው- የስ-ነልቦናና የህግ ምሁራን

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህፃናትን ለጦርነት የሚያሰማራውን የአሸባሪውን ህወሓት ቡድን በጦር ወንጀለኝነት ለማስጠየቅ ስራዎችን መጀመር እንደሚገባ የስ-ነልቦናና የህግ ምሁራን ተናገሩ፡፡

የአዲስ አበባ ህፃናት በበኩላቸው እኩዮቻቸው በአሸባሪው ቡድን ለጦርነት መማገዳቸውን ኮንነዋል፡፡

ህፃናቱ እኩዮቻችን የወላጆቻቸውን ጥበቃና ድጋፍ በሚፈልጉበት ጊዜ፣ መማር ባለባቸው ወቅት ወደ ግጭት ቀጠና መግባታቸው ያልተገባ መሆኑን በመግለፅ ጦር መሳሪያ ሳይሆን ደብተርና እስክርቢቶ እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

የስነልቦና ባለሙያው ሳሙኤል ካሳሁን ህፃናት በግጭት ውስጥ መሳተፋቸው በድህረ ግጭትም ለስ-ነልቦና
ጫናና ለሰብዓዊ ቀውስ እንደሚዳርጋቸው ገልፀው ችግሩን ለማስቆም ሀገር በቀልና የውጭ ሰብዓዊ ድርጅቶች መስራት አለባቸው ነው ያሉት።

አክለውም የተከፈለው መስዕዋትነት ተከፍሎ በአጭር ጊዜ ውስጥ ህግ በማስከበር ግጭቱን ማስቆም ይገባል ብለዋል።

የህግ ምሁሩ አብዱረዛቅ ነስሩ በበኩላቸው አሸባሪው ቡድን ህፃናትን ወደ ጦር ማሰማራቱ ከዓለም አቀፍ ስምምነቶች፣ ከአፍሪካ ቻርተርና ከኢፌዲሪ ህገመንግስት የሚጣረስ መሆኑን በመግለፅ በዓለም አቀፍ የጦር ፍርድ ቤት ሊጠየቅ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ችግሩ በዋናነት የትግራይ ህዝብን ተጎጂ የሚያደርግ መሆኑን እያንዳንዱ ትግራዋይ በማወቅ ልጆቹ ወደ አውደ ውጊያዎች እንዳይሄዱ ሊቃወም ይገባዋልም ነው ያሉት።

በአፈወርቅ እያዩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.