Fana: At a Speed of Life!

ዘማቾች ጠላቶቻቸውን ድል አድርገው ይመለሳሉ – የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀንአ ያደታ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ዘማቾች ጠላቶቻቸውን ድል አድርገው ይመለሳሉ ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀንአ ያደታ ገለጹ፡፡

‘‘ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ፤ የወጣቶች ሽኝትና የድጋፍ ርክክብ የትም፣ መቼም በምንም’’ በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው መርሃግብር ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል፡፡

በንግግራቸውም ኢትዮጵያ እስካሁን ሉዓላዊነቷን ጠብቃ መኖሯን አውስተዋል፡፡

ህወሃት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶችን እየፈጸመ፣ ኢትዮጵያውያንን በቋንቋ በሃይማኖት፣ በብሄር እያከፋፈለ የኖረ የጥፋት ቡድን መሆኑን ገልጸው፥ ይህ አልበቃ ብሎት ሃገሩን ድንበሩን በሚጠብቀው የሃገር መከላከያ ሰራዊቱ ላይ ያደረሰውን ግፍ አስታውሰዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም የትግራይ ህጻናትን በማስገደድ ወደጦርነት እያስገባ መሆኑን ያብራሩት ዶክተር ቀንአ፥ ፈቃደኛ ያልሆኑትን ደግሞ እየገደላቸውም ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ጁንታው ይሄ አልበቃ ብሎት ከውጭ ሃይሎች ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሰሩ የሚገኙ ቢሆንም፥ ይህ የማይሆን ቅዠት ነው ብለዋል፡፡

ወጣቶችና ዘማቾች እንዲሁም መላው ኢትዮጵያዊ እያደረገ ላለው ሁሉን አቀፍ ድጋፍም አመስግነዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.