Fana: At a Speed of Life!

በባህርዳር ከተማ የሚኖሩ የቀድሞ ምልስ ሰራዊት አባላት  የክተት ዘመቻውን  ለመቀላቀል ሽኝት ተደረገላቸው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህርዳር ከተማ የሚኖሩ የቀድሞ ምልስ ሰራዊት አባላት የተደረገውን የክተት ዘመቻ ለመቀላቀል አሸኛኘት ተደረገላቸው፡፡

ከዚህ በፊት የሀገርን ዳር ድንበር ሲያስከብሩ ቆይተው እና ግዳጃቸውን አጠናቀው በመመለስበ ባህርዳር በልዩ ልዩ የስራ ዘርፎች ተሰማርተው የነበሩ የቀድሞ የመከላከያና ልዩ ኃይል አባላት በክልላችን ብሎም በሀገራችን የተጋረጠውን ውስጣዊና ውጫዊ ወረራ ለመከላከል በክልሉ መንግስት የተደረገውን የክተት ዘመቻ በደስታ ተቀብለው መቀላቀላቸውን ተናግረዋል፡፡

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉ  ÷ በትግራይ ክልል አጎራባች የሚኖሩ የአማራ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በትህነግ የግፍ አገዛዝ ውስጥ በመቆየታቸውና በኖሩበት ክልል እንደባይተዋር ተቆጥረው ቦታቸውን ፣ልማታቸውንም ሆነ ሀብታቸውን ለዘመናት ተነጥቀው መቆየታቸውን ገልፀዋል፡፡

አሁን በተደረገው ፍትህ የማስፈን ተግባር የተመለሰላቸውን የማንነት ጥያቄ ለመቀልበስ ህወሓት እየታተረ ይገኛል ማለታቸውን ከባህርዳር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በመሆኑም ጀግናው የመከላከያም ሆነ የልዩ ኃይልና ሚሊሻ እያደረገ ያለው የሀገርን ክብር የማስጠበቅ ተጋድሎ በድል እንዲጠናቀቅ የሁላችንም አጋርነት አስፈላጊ በመሆኑ የክልሉ ምንግስት የክተት ጥሪ ማስተላለፉን ገልፀዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም የባህርዳር ከተማ ምልስ ሰራዊት አባሎቻችን ጥሪውን ተቀብለው ወደ ሰላም ማስከበር ግንባር ለመሄድ በመወሰናቸው የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ በድል እንዲመለሱ መልካም ምኞታቸውን ገልፀውና የሀገር ክብር መገለጫ ሰንደቅዓላማ አስረክበው ሸኝተዋቸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.