Fana: At a Speed of Life!

ከደረጃ በታች የሆነ 3ሺህ 685 ነጥብ 2 ሜትሪክ ቶን ምርት ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ ታገደ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ከደረጃ በታች የሆኑ 3ሺህ 685 ነጥብ 2 ሜትሪክ ቶን የተለያዩ ገቢ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታግደዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በተጠናቀቀው የ2013 በጀት ዓመት አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ የወጣላቸውን ምርቶችና አገልግሎቶች ጥራታቸው፣ ደህንነታቸውንና ትክክለኛነታቸውን ለማረጋገጥ በተከናወነ ስራ ብዛቱ 3ሺህ 685 ነጥብ 2 ሜትሪክ ቶን ምርቶች ነው የታገዱት፡፡
የኬሚካል ምርቶች፣ የኤሌክትሪክ እና የኮንስትራክሽን እቃዎች እንዲሁም የታሸጉ ምግቦች ከደረጃ በታች ሆነው በመገኘታቸው ነው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የተደረገው፡፡
በተመሣሣይም ዳይሬክቶሬቱ በ685ሺህ 500 ሜትሪክ ቶን የወጪ ምርቶች ላይ የኢንስፔክሸን ሥራ ለማከናወን አቅዶ በ620 ሺህ 760 ነጥብ 5 ሜትሪክ ቶን የወጪ ምርቶች ላይ የኢንስፔክሽን ሥራ በማከናወን ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ዳይሬክቶሬቱ ወካይ ናሙናዎችን ለኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት በመላክ ከሚያደርገው የላብራቶሪ ፍተሻ እና የኢንስፔክሽን ስራዎች በተጨማሪ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የውሃ ፓምፕና የሶላር ቴክኖሎጂ ምርቶችን በሦስተኛ ወገን ዓለም አቀፍ የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እያቀረቡ እንዲስተናገዱ አድርጓል፡፡
በአጠቃላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የወጪና ገቢ ዕቃዎች ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት በበጀት አመቱ በሁሉም ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የኢንስፔክሽን ስራዎችን በማከናወን የኢትዮጲያን ደረጃ ያሟሉ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ወይም ከሀገር እንዲወጡ ፍቃድ መሰጠቱን ከንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በአንጻሩ አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃን ያላሟሉ የገቢ ምርቶች ደግሞ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ በማድረግ የህብረተሰቡን ጤና እና የአካባቢን ደህንነትን ከጉዳት መታደግ መቻሉም ነው የተገለጸው፡፡
በመጨረሻም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ ለማከናወን ካቀደው የኢንስፔክሽን ሥራ 97 ነጥብ 7 በመቶ ያህሉን እንዳሳካ በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.