ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና ዶ/ር ቀንአ ያደታን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ አመራሮች ደም ለገሱ
አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነአ ያደታን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ለመከላከያ ሰራዊቱ ደጀንነታቸውን ለማሣየት ደም ለግሰዋል፡፡
“ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ” በሚል መርህ ዛሬ በመስቀል አደባባይ የመከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ርክክብ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
በመርሃግብሩ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር ቀነአ ያደታ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ ፣ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ጀነራሎች እና ሌሎችም የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለግሰዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!