Fana: At a Speed of Life!

ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የኦክስጅን ማምረቻ ሊቋቋም ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ከፌዴራል መንግስት በተገኘ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የንግስት ኢሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኦክስጅን ማምራቻ እንደሚቋቋም ዩኒቨርሲቲዉ አስታወቀ፡፡

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሀብታሙ አበበ እንደገለጹት፥ በሆስፒታሉ እስከ 2011 ዓ.ም ድረስ በነበረው ሂደት የህክምና መሣሪያ አቅርቦትን ጨምሮ በርካታ ችግሮች ነበሩ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሆስፒሉ አዳዲስ የማስተማሪያና አገልግሎት መስጫ ህንፃዎችን በማስገንባት እና ያልተሟሉ የህክምና መሣሪያዎችን ግዢ በመፈፀም በአሁኑ ጊዜ የአገልግሎት አሰጣጡን ለህብረተሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ለአብነትም የሲቢሲ እና የኤክስሬይ ማሽኖች ግዥ ተፈጽሞ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ሲሆን፥ ተጨማሪ የሲቲ ስካንና የኤም.አር.አይ ማሽኖች ተገዝተው እየመጡ መሆናቸዉም ተገልጿል፡፡

ከፌዴራል መንግስት በተገኘዉ ከ1ቢሊየን በሚበልጥ ወጪ በሆስፒታሉ ኦክስጅን የማምረት ስራ ለማስጀመር በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኙም ዶክተር ሀብታሙ ማስረዳታቸውን ኢሬቴድ ዘግቧል፡፡

ኦክስጅን የማምራቱ ሂደት ሲጠናቀቅም ከ540 በላይ ለሚሆኑ ተካሚዎች በቀጥታ ኦክስጅን መስጠት እንደሚያስችልም አመላክተዋል፡፡

በተጨማሪም በአካባቢዉ ለሚገኙ ሌሎች የጤና ተቋማትም ኦክስጅን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚረዳ ጠቅሰው፥ ድጋፍ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.