ዶ/ር ሙሉ ነጋ እንዲሁም ከ25 ዩኒቨርስቲዎች የተወጣጡ አመራሮች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አከናወኑ
አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሙሉ ነጋ እንዲሁም ከ25 ዩኒቨርስቲዎች የተወጣጡ አመራሮች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዋናዉ ግቢ አካሄዱ፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድና ስልጠናዊ ግምገማ እያካሄደ ይገኛል።
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሚካሄደው ይህ ስልጠናዊ የግምገማ መርሃ ግብር ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሃምሌ 29 ቀን 2013ዓ.ም እንደሚቆይ ተገልጿል፡፡
በሰላማዊት ተስፋዬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!