Fana: At a Speed of Life!

ህወሓትን ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናችውን 5 የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ህወሓትን ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናችውን የኢትዮጵያ ነጻነት ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ ራያ ራዩማ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲና ህዳሴ አስታወቁ፡፡
 
ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ጉዳዩን አስመልክተው በዛሬው ዕለት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
 
በመግለጫቸውም አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናችውን ነው የገለጹት፡፡
 
ህወሓት ካልተወገደ ሀገር ሰላም ስለማትሆን የትግራይ ህዝብም በአሸባሪ ቡድኑ የሚደርስበት ስቃይ ሊቆምለት ይገባል ነው ያሉት፡፡
 
በህዝቡ ላይ የሚደርሰውን በደል ለማስቆምና የከፈተውን ጦርነት ለማስቆም በቅንጅት እንደሚታገሉ አስታውቀዋል፡፡
 
አሸባሪው ቡድን ከአፈጣጠሩ ጀምሮ የጭቁን ህዝቦች እፎይታና ሰላም የማይሻና ዘወትር በሰው ደም እየነገደ በስልጣን መቆየትን የሚፈልግ ድርጅት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
 
የትግራይ ህዝብ ከአሸባሪው ድርጅት ያተረፈው ችግር እና እልቂት እንጅ አንዳችም ያተረፈው ነገር የለም ያሉት ፓርቲዎቹ ÷የትግራይን ህዝብ እንደ መሸሸጊያ ተጠቅሞ በአሁኑ ሰአት መንግስት የወሰደውን የተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት ወደ ኋላ በመተው በሶስት አቅጣጫ ትንኮሳ ከፍቶ ሀገር ለማፍረስ እየሰራ ነው ብለዋል።
 
በትንኮሳው ህጻናት፣ ሴቶች፣ አረጋውያን እና የሃይማኖት አባቶችን ከፊት ለፊት በማስቀደም የአለም አቀፍ ህግ የማይፈቅደውን ከ15 ዓመት በታች የሆኑትን ህጻናት በማሰልፍ የተለያዩ አደንዛዥ እጾችን በመጠቀም ውጊያ እያካሄደ ነው ብለዋል፡፡
 
በመሆኑም መንግስት ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል ይህንን አሸባሪ ቡድን ለመደምሰሰ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
 
በምንይችል አዘዘው
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.