የትህነግ ቡድን በመቃወምና ለመከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የጸጥታ አካላት ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ የአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ያሉ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ነዋሪዎች ወደ መስቀል አደባባይ እየተጓዙ ነው
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የትህነግ ቡድን በመቃወምና ለመከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የጸጥታ አካላት ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ የአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ያሉ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ነዋሪዎች ወደ መስቀል አደባባይ እየተጓዙ ይገኛሉ፡፡
የቡራዩና ዙሪያ ነዋሪዎች አሸባሪው የትህነግ ቡድን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለማውገዝ እና ለመከላከያ ሰራዊት እና ለሌሎች የሃገርን ህልውና ለማስጠበቅ ለተሰማሩ የፀጥታ አካላት ያላቸውን ድጋፍ ለመግለፅ ወደ መስቀል አደባባይ ጉዞ እያደረጉ ነው፡፡

የሰበታ ከተማ እና አካባቢዋ ወጣቶች መስቀል አደባባይ በሚካሄደው ሰልፍ ለመሳተፍ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ እየተጓዙ ነው::
በተመሳሳይ የሱሉልታ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደሮችና ነዋሪዎች ለሃገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸዉን ድጋፍ ለመግለጽና የአሸባሪዉን ሕወሃት ጸረ ኢትዮጵያ እንቅስቃሴ ለመቃወም ወደ መስቀል አደባባይ እያመሩ እንደሚገኙ የዘገበው ኦቢኤን ነው::
ሰልፈኞቹ ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ ሰልፉ ላይ ለመሳተፍ እየተጓዙ ነው፡፡