Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት ሀገር የማፍረስ አቅምና ብቃት የለውም – አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪው ህወሓት ሀገር የማፍረስ አቅምና ብቃት የለውም ሲሉ የሶማሊ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ገለጹ፡፡

ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ ይሄን ያሉት በሻለቃ ከደር መሀሙድ የውትድርና ማሰልጠኛ ማዕከል ሲሰልጥኑ የነበሩ የሶማሊ ክልል ሚሊሺያ ምረቃ ስነስርዓት ላይ ነው፡፡

በምርቃው ስነስርዓት ላይ የሶማሊ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድን ጨምሮ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ሁሴን ሃሺ፣የሶማሊ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ፣ የሶማሊ ክልል ልዩ ሀይል አዛዥ ም/ኮ መሀመድ አህመድ፣ የሶማሊ ክልል ፖሊስ ኮምሽነር፣ የዞን አስተዳደሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የሶማሊ ክልል የሰላምና ደህንነት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ሁሴን ሃሺ በዚህ ወቅት እንደገለፁት÷ ዛሬ የተመረቁት ሚሊሺያዎች የክልሉን ሰላም ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት ላይ የጎላ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ብለዋል።

የሶማሊ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ በበኩላቸው ከለውጡ በኋላ እንደ ክልል ትላልቅ ድሎች እንደተመዘገቡ ገልፀው÷ ከድሎቹ መካከልም በክልሉ የሰፈነው አስተማማኝ ሰላም አንዱ እንደሆነ ተናግረዋል።

አቶ ሙስጠፌ መሃመድ የክልላችን መሠረት ሰላም እና መረጋጋት ነው ያሉ ሲሆን÷ አሸባሪው የህወሀት ታጣቂ የሶማሊ ክልልን ለማተራመስ የተለያዩ ሴራዎችን እየሸረበ እንደሆነና ይህንን ሴራ እንደሚመከት እርግጠኛ ነኝ ብለዋል።

አሸባሪው ህወሃት ሀገር የማፍረስ አቅምና ብቃት እንደሌለው ገልፀው÷ የለመደውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ሁሉም ዜጋ መታገል አለበት ማለታቸውን ከክልሉ ምንገስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው÷ ዛሬ ለምረቃ የበቃችሁት የሀገራችሁንና የክልላችሁን ሰላም ለመጠበቅ ስለሆነ በጎሳ ስም ህዝብን ከህዝብ የማጋጨት ስራን የሚሰሩ ሰዎች መታገል አለባችሁ ብለዋል።

ሰልጣኞቹ በስልጠና ወቅት የኢትዮጵያንና የክልሉን ህገመንግስት፣ የሰበዓዊ መብት አያያዝ፣ የመሣሪያ አጠቃቀምና ሌሎች ስልጠናዎችን የወሰዱ ሲሆን÷ በክልሉ ወረዳዎች እንደሚመደቡ ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.