Fana: At a Speed of Life!

በአልጄሪያ የሰደድ እሳት አደጋ የ42 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አልጄሪያ ውስጥ በተነሱ የሰደድ እሳት አደጋዎች እስካሁን የ42 ሰዎች ሕይወት እንዳለፈ ተገለፀ፡፡

የ25 ወታደሮች ሕይወት የተቀጠፈው በካቢሊ ተራራማ አካባቢ ባለ ጥቅጥቅ ደን ውስጥ የተከሰተውን ሰደድ እሳት ለማጥፋት ሲሰሩ እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡

ወታደሮቹ ሕይወታቸውን መስዋዕት ቢያደርጉም የ100 ሰዎችን ሕይወት ታድገዋል ነው የተባለው፡፡

በዚህ አካባቢ በሕይወት ላይ የደረሰው አሳዛኝ አደጋ በሀገሪቷ ከደረሱ መሰል አደጋዎች ሁሉ የከፋው ነው ተብሏል፡፡

ለሰደድ እሳት አደጋዎቹ መከሰት ተቀጣጣይ ቁሶች መንስኤ ሳይሆኑ እንዳልቀረም ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት፡፡

ምንጭ÷ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.