አሸባሪውን የህወሃት ቡድን ለመደምሰስ በንቃት አካባቢያችንን በመጠበቅ ላይ ነን-የውጫሌ ከተማ የፀጥታ ሀይሎች
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪውን የህወሃት ቡድን ለመደምሰስ በንቃት አካባቢያቸውን በመጠበቅ ላይ መሆናቸውን በደቡብ ወሎ ዞን የውጫሌ ከተማ ታጣቂዎችና የፀጥታ ሀይሎች አረጋገጡ።
የአሸባሪው ቡድን የላካቸውን ሰርጎ ገቦች ግብዓተመሬት ለመፈፀም ዝግጁነት አለንም ብለዋል።
የቀድሞ ሰራዊት አባላት፣ ወጣቶች፣ ሚሊሻዎች፣ በክተት ከሌሎች አካባቢዎች የመጡ ወዶ ዘማቾች ቀጠናቸውን ከጠላት ለማፅዳት ከመከላከያ ሰራዊት በመስራት ላይ ናቸው።
የግልና የቡድን መሳሪያዎችን በመያዝም ወራሪውን ለመመከት እየሰሩ እንደሆነ ነው የተናገሩት።
አሸባሪው የህወሃት ቡድን ዳግም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የባርነት ቀንበርን ለመጫን ያደረገው ትንኮሳ በኢትዮጵያዊያን የተባበረ ክንድ ለመመከት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።
ህዝቡ በሀሰተኛ ወሬና የጁንታው ፕሮፖጋንዳ ከመፈታት ይልቅ አንድነቱን በማጠናከር የአሸባሪውን ግብአተ መሬት እንዲያፋጥንም ጥሪ አቅርበዋል።
በአፈወርቅ እያዩና ለይኩን ዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!