የእግረኛ መንገዶችን ለጉዳት በዳረጉ አካላት ላይ እርምጃ ተወሰደ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በእግረኛ መንገዶች ላይ ጉዳት ባደረሱ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገለፀ፡፡
በባለስልጣኑ የማዕከላዊ አዲስ አበባ መንገድ ሐብት አስተዳደር በአቧሬ አደባባይ እና በተለምዶ አሮጌው ቄራ ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች በእግረኛ መንገድ ላይ የተቀመጡ የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶችን አስነስቷል፡፡
የእግረኞችን የመንቀሳቀስ መብት በሚጋፋ መልኩ ህገወጥ ተግባራት በሚፈፅሙ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ ባለሥልጣኑ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ የጀመረውን ህግ የማስከበር ሥራ አጠናክሮ መቀጠሉ ነው የተገለፀው፡፡
በዚህም ለደረሰው ጉዳት ካሳ የማስከፈል እና አጥፊዎችን በህግ እስከ መጠየቅ የሚያደርስ እርምጃ በመውሰድ መንገዱን ለትራፊክ ክፍት የማድረጉን ስራ በተለያዩ አካባቢዎች እየሠራም ነው ተብሏ፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ህብረተሰቡ መንገዶች የጋራ ሀብት መሆናቸውን ተገንዝቦ፣ ከማንኛውም ህገ ወጥ ድርጊት እንዲጠብቃቸውና ህገ ወጥ ድርጊት ተፈፅሞ ሲያገኝም በነፃ የስልክ መስመር 8267 ወይም በአቅራቢያው በሚገኘው የመንገድ ሀብት አስተዳደር ፅህፈት ቤት እንዲያሳውቅ ጥሪ ማስተላለፉን ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!