በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ስም የተሰየመው የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ስም የተሰየመው የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተመረቀ፡፡
የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሃሰን የሱፍ ÷ የትምህርት ቤቱ ዓላማ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ በህይወት ዘመኑ የሰራውን የጥበብ ስራ ለትውልድ ማስተላለፍ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
መጪው ትውልድም በኪነ ጥበቡዙሪያ የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ሁኔታዎችን ማመቻቸት መሆኑም ተነግሯል፡፡
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ አባ ገዳዎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በሌላ በኩል ዩኒቨርሲቲው በነገው ዕለት ለ16ኛ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ያስመርቃል፡፡
በኤፍሬም መልካሙ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!