Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የገጠማትን የሕልውና አደጋ ለመመከትና የመፍትሄ አካል ለመሆን የዲያስፖራ አባላት ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የገጠማትን የሕልውና አደጋ ለመመከት በምታደርገው ጥረት ውስጥ የመፍትሄ አካል ለመሆን ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ 500 የዲያስፖራ አባላት ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው።
የዲያስፖራ አባላት ከጳጉሜ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሏል።
ዲያስፖራዎቹ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት አገሪቷ የገጠማትን የውስጥና የውጭ ፈተና በጋራ ለመካፈል፣ ችግሮቹን ለመመከትና የመፍትሄው አካል ለመሆን ነው ተብሏል።
የዲያስፖራ አባላቱ በቆይታቸው ለአገር የሚጠቅሙ የተለያዩ ተግባራትን እንደሚያከናውኑ የኢትዮጵያ የዲያስፖራ የተግባር ምክር ቤት ተወካይ አቶ ፍቃዱ አባይ ገልጸዋል።
“ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ የትም፣ መቼም፣ በምንም” የሚለውን ጥሪ በመቀበል÷ ዲያስፖራው ከመከላከያ ጎን መቆሙን ለማሳየት የደም ልገሳ መርሃ ግብር እንደሚካሄድም ተናግረዋል።
የአሸባሪው ሕወሓት አገር ለማፍረስ የሚያደርገውን እኩይ ተግባርና የውጭ ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሠላማዊ ሰልፍ በመስቀል አደባባይ እንደሚካሄድም ጠቁመዋል።
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የተመሰረተበትን 10ኛ ዓመትና ሁለተኛ ዓመት የውሃ ሙሌት የተከናወነበት ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግም ዲያስፖራው ግድቡን እንደሚጎበኙ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.