በሰበታ ከተማ መከላከያ ሰራዊትን ለመደገፍ የማህበረሰብ ስፖርት እንቅስቃሴ ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሰራዊትን ለመደገፍ እና የሽብር ቡድኖችን ህወሓት እና ሸኔን ለማውገዝ በሰበታ ከተማ የማህበረሰብ ስፖርት እንቅስቃሴ ተካሂዷል፡፡
መርሃ ግብሩን የኦሮሚያ ስፖርት ኮሚሽን እና የሰበታ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን በጋራ አዘጋጅተውታል፡፡
ስፖርታዊ እንቅስቃሴው ”የሀገራችን ስም፣ ዝና እና ክብር ለማስጠበቅ ለመከላከያ ሰራዊት ዘብ እንቆማለን!”በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው።
በመድረኩ በባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ምክትል ዴኤታ አቶ ሃብታሙ ሲሳይን ጨምሮ የኦሮሚያ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ነስር ሁሴን፣ የሰበታ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ብርሃኑ በቀለ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ።
በተካሄደው የማህበረሰብ ስፖርት እንቅስቃሴ ላይ አትሌቶች ፣ የሰበታ ከተማ ነዋሪዎች እና ወጣቶች የእግር ጉዞ፣ የደም ልገሳ እና የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነወ መረጃ ያመላክታል፡፡
ከዚህ ባለፈም በሁሉም ጾታ ከተለያዩ የአትሌቲክስ ክለቦች የተወጣጡ አትሌቶች የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ በማድርግ ለመከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አጋርነት አሳይተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!