Fana: At a Speed of Life!

የወልቂጤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በወልቂጤ ከተማ የክልሉን 3ኛ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ሥራ አስጀምረዋል፡፡

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዜጎች በአንድ ቦታ ብዙ አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ፣ ጊዜና ወጪ እንዲቆጥቡና የአገልግሎት ጥራት እንዲሻሻል የሚያስችል ሥርዓት ነው።

በተቀናጀ መረጃ አሰጣጥ የዜጎችን እርካታ በማሳደግና የመንግሥት ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ተመላክቷል፡፡

የወልቂጤ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በውስጡ 6 ተቋማት የያዘ ሲሆን÷ በአጠቃላይ 42 የተለያዩ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

ከፍተኛ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ያለባቸው፣ ተገልጋይ የሚበዛባቸው፣ ለሙስናና ብልሹ አሠራር የተጋለጡ እንዲሁም ቅሬታ የሚበዛባቸው ተቋማት ተለይተው ወደ ማዕከሉ እንዲገቡ ተደርጓል።

ተቋማትን ከወረቀት ንክኪ ነጻ እና በውጤት ወደሚለካ አሠራር ለማሸጋገር እየተተገበሩ ካሉ የለውጥ ሥራዎች መካከል “የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት” ተጠቃሽ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.