Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ ኮሪያ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአምስት የአፍሪካ ሀገራት የምግብ ድጋፍ የሚውል 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር ለገሰች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ ኮሪያ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአምስት የአፍሪካ ሀገራት የምግብ ድጋፍ የሚውል 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር መለገሷን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።
የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከደቡብ ኮሪያ የተገኘው የገንዘብ ድጋፍ ለኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ ፣ማዳጋስካር ፣ደቡብ ሱዳንና ቡርኪናፋሶ ተረጂዎች ሰብአዊ እገዛ ይውላል ብሏል።
የዓለም የምግብ ፕሮግራም የምዕራብ አፍሪካ አካባቢ ዳይሬክተር ክሪስ ኒኮይ በቡርኪናፋሶና በናይጄሪያ እርዳታ ጠያቂዎች ስም ከደቡብ ኮሪያ ህዝብና መንግስት ለተደረገው ወቅቱን የጠበቀ ልገሳ እናመሰግናለን ብለዋል።
የዓለም የምግብ ፕሮግራም የደቡባዊ አፍሪካ አካባቢ ዳይሬክተር መንግስተአብ ሃይሌ ሰዎች ለርሃብ እንዳይጋለጡ ስጋት እንዳለ ገልጸዋል።
ከኮሪያ ህዝብና መንግስት የተገኘው ልገሳ ወቅቱን የጠበቀ ከመሆኑም በላይ በህብረተሰቡ ህይወት ውስጥ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጣ ነው ማለታቸውን የድርጅቱ መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.