Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዘርፉ ላደረገው ድጋፍ ተደነቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ለአየር ትራንስፖርቱ የምታደርገውን ድጋፍ አደነቀ፡፡

ማህበሩ በአስከፊው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት ኢትዮጵያ ስታደርገው የቆየችውን ድጋፍ አድንቆ÷ ይህን እንድትቀጥልም ጠይቋል።

ዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር የአፍሪካና የመካከለኛው ምሥራቅ ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት ካሚል አላዋዲ በበኩላቸው÷ “ኢትዮጵያ የጉዞ እና የአየር አገልግሎት ትስስርን ለማሳደግ በወሰደችው አዎንታዊ እርምጃዎች እንኳን ደስ አለን” ብለዋል።

እንደአብነት የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት የወሰዱ ተጓዦችን ያለገደብ መቀበሏን አንስተው÷ እነዚህ እርምጃዎችም ኢትዮጵያ በአየር ትራንስፖርት ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ኢኮኖሚዋ ላይ እንደረዳት ጠቅሰዋል።

በዚህም ኢትዮጵያ በአጠቃላይ የአፍሪካን ከአማካይ በላይ ማስመዝገቧም ነው የተጠቀሰው።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰጠው የቀጥታ በረራና የአፍሪካ ህብረት ያስቀመጠው የቀጥታ በረራ አገልግሎት ለ21 ሺህ ሰዎች የስራ ዕድል ፈጥሯል።

በዚህም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የ81 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ጭማሪ አሳይቷል።

በሌላ በኩል በኢትዮጵያም ሆነ በመላው አፍሪካ ክትባት መውሰድን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ማህበሩ አስምሮበታል።

ምንጭ፡- ኢንጂነሪንግ ኒውስ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.