Fana: At a Speed of Life!

የአሰላ ከተማን የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች በ6 ወራት ይጠናቀቃሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ1.4 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውና የአሰላ ከተማን የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችሉ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች በስድስት ወራት ግዜ ውስጥ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ የከተማው ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት አስታወቀ ::

ከሁለት ዓመታት በፊት ቁፋሯቸው የተጀመረው እነዚህ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁም ለ 350 ሺህ ነዋሪዋችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚያስችሉ የከተማው ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት አስታውቋል::

በዛሬው እለትም የፕሮጀክቶቹን የግንባታ ሂደት የሚቃኝ የመስክ ጉብኝት የተካሔደ ሲሆን፤ የኦሮሚያው ሃና ኢነርጂ ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ኢነጂነር ሀብታሙ ኢተፋን ጨምሮ አምባሳደር ኢንጂነር ሽፈራው ጃርሶም በጉብኝቱ ተሳትፈዋል።

በከተማዋ ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ በ16.5 ሚሊየን ብር ወጪ 10 ዘመናዊ የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች ግንባታቸው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት መዘጋጀታቸው ተጠቁሟል።

በጋሻው አርጋው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.