የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ወረራ ከዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሰተዳደር የተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ተፈናቃዮቹ በሚገኙበት እብናት ከተማ ጊዜያዊ መጠለያ በመገኘት ድጋፉን አስረክቧል፡፡
በእብናት ከተማ የተደረገው ድጋፍ ግማሹ በደሴ ከተማ ለተጠለሉ ተፈናቃዮች እንዲደርስ የታሰበ ቢሆንም በደቡብ ወሎ ድጋፉን ከሚያስተባብሩ አካላት ጋር በነበረው ውይይት በእብናት እየጨመረ ከመጣው እና ካለው ተፈናቃይ ቁጥር አንፃር ለዋግና አካባቢው ተፈናቃይ ወገኖች እንዲደርስ መወሰኑን ነው ዩኒቨርሲቲው የገለጸው፡፡
ዩኒቨርሲቲው እና የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች ከዚህ ቀደም በደባርቅ ግንባር እና በጋይንት ግንባር ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
ወደፊትም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሰለሞን ፋንታው መግለጻቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!