Fana: At a Speed of Life!

ከአዲሱ መንግስት ለህዝቡ መሰረታዊ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ አመራር እንጠብቃለን አሉ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፋ ቢ ሲ) የፊታችን መስከረም 24 ከሚመሰረተው አዲስ መንግስት ለህዝቡ መሰረታዊ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ አመራር እንጠብቃለን ሲሉ በሰሜን ሸዋ ዞን የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ።
በአረርቲ ከተማ ካነጋገርናቸው ነዋሪዎች መካከል ወጣት ሙሉነህ ተሰማ፣ መምህርት ስመኝ ካሳ፣ የዓለም ዋስ እና አማረ መንግስቱ ለፋና ደብረ ብርሃን ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፥ አዲስ የሚቋቋመው መንግስት በአሸባሪው ህወሃት የተከፈተውን ጦርነት በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ሰላም ማስጠበቅ ላይ ቀዳሚ ትኩረት አድርጎ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው መልሶ ማቋቋም እና የኑሮ ውድነትን በማረጋጋት በኩል ተጨባጭ ስራዎችን እንዲያከናውን እንደሚሹም ገልፀዋል ነዋሪዎቹ።
አንዳንድ የውጭ ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ እያሳደሩት ያለውን ጫና ለመቋቋም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን በእውቀት እና በብስለት መፈፀም ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል።
በህዝብ የተመረጡ ተሿሚዎችም ስር የሰደዱ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በአገልጋይነት መንፈስ መፍታት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
በሰላም አሰፋ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.