ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በባሕር ዳር ዘንዘልማ ቀበሌ የመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በአሸባሪው ትህነግ ወረራ ምክንያት ከዋግኸምራ ተፈናቅለው በባሕር ዳር ዘንዘልማ ቀበሌ የመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ጎበኙ፡፡
ርእሰ መስተዳድሩ ከተፈናቃዮች ጋርም ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱም ተፈናቃዮቹ የአካባቢያቸው ሰላም ተመልሶ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ መንግሥት እንዲሠራ ጠይቀዋል፡፡
ርእሰ መስተዳድሩ ዶክተር ይልቃል ሰላም ተፈጥሮ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማድረግ መንግሥት በትኩረት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በውይይቱ ወጣት ተፈናቃዮች ወደ ትግሉ በመቀላቀል አሸባሪውን ቡድን በመደምሰስ እንዲሳተፉም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ተፈናቃዮችን መንግሥት በሚችለው መጠን እያገዘ እንደሆነ የተናገሩት ርእሰ መስተዳድሩ የአካባቢው ሕዝብም አስፈላጊውን እገዛ ለተፈናቃዮቹ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ዶክተር ይልቃል ከፋለ በባሕር ዳር ከተማ የሚገኘውን የአማራ ብረታብረት ኢንዱስትሪ እና ማሽን ቴክኖሎጅ ልማት ኢንተርፕራይዝንም ጎብኝተዋል።
ኢንተርፕራይዙ በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገባ የክልሉ መንግሥት ድጋፍ እንደሚያደርግም ማረጋግጣቸዉን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን