Fana: At a Speed of Life!

በጌዴኦ ዞን የጣለው ከባድ ዝናብ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በጌዴኦ ዞን ይርጋ ጨፌ ወረዳ ጭቶ፣ ዶማርሶና ቡዱቅሳ በሚባሉ ቀበሌዎች በጣለው ከባድ ዝናብ የአንድ ሰዉ ህይወት ሲያልፍ 39 አባወራዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ተገለፀ፡፡

የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዮሐንስ ታደሰ÷ ትናንት በጣለዉ ከባድ ዝናብ 39 አባወራዎች ከ156 የቤተሰብ አባላት ጋር እንደተፈናቀሉ ገልፀዋል፡፡

ከቤት ንብረት የተፈናቀሉት አባወራዎች በቤተሰቦቻቸውና በጎረቤት መጠለላቸውን አስተዳዳሪ በመናገር በአሁኑ ጊዜ የነፍስ አደን ሥራ እየተሰራ ሲሆን÷ አደጋ በደረሰበት አካባቢ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አስተዳዳሪዉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.