Fana: At a Speed of Life!

ፖሊስ ለኢትዮጵያውያን ምስጋናውን አቀረበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ከፀጥታ እና ደህንነት ግብረ ሃይል ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚህም ከስደስተኛው ሃገራዊ ምርጫ አንስቶ የዘመን መለወጫ፣ የመስቀል በዓል( በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች) ፣የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባና በቢሾፍቱ ፣ የመንግስት ምስረታ የበዓለ ሲመት ስነ ስርዓት ያለ ጸጥታ ችግር መጠናቀቃቸውን የፈደራል ፖሊስ አስታወቀ።
ዛሬ በተሰጠው መግለጫም ግብረ ሃይሉ በግልጽ እቅድ ላይ ተመስርተው ስራቸውን ሰርተዋል ብለዋልም ።
ያለፉት ሁነቶች ያለአንዳች ችግር መጠናቀቃቸው በተቋማት መካከል ተናቦ የመስራት ልምድ የተገኘበት አጋጣሚን ፈጥሯልም ነው ያሉት ኮሚሽነር ጀነራሉ።
በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚፈጠረው የመንገዶች መዘጋት ህብረተሰቡ ላሳየው ትዕግስትም የተለያዩ የፖሊስ አባላትና የደህንነት አባላት ሃገራዊ እና ህዝባዊ ሃላፊነታቸውን በሚገባ ተወጥተዋል ተብሏል።
ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችም በተልዕኮው ውስጥ ተግባራዊ ሆነዋል።
እነዚህን ሁነቶች ለማደናቀፍ ጥረት ሲያደርጉ የህወሓት የሽብር ቡድንና እና የሸኔ ቡድን ተልዕኮ የተሰጣቸው ግለሰቦች በአዲስ አበባ በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተገልጿል።
በግለሰቦቹ እጅ ላይም የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች የተያዙ ሲሆን፥ ጉዳዩ ምርመራ እየተደረገበት በመሆኑ በቀጣይ መረጃው ለህዝቡ ይፋ ይሆናል ተብሏል።
በምስክር ስናፍቅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.