የኑሮ ውድነትን ባባባሱ የንግድ ተቋማት ላይ ሕጋዊ እርምጃ ተወሰደ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ ከተማ የኑሮ ውድነቱን በሚያባብሱ የንግድና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ በተወሰደ እርምጃ 113 የንግድ ቤቶች መታሸገቸውን የከተማ ዋ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡
ወቅቱን ተገን አድርገው የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሠዱን የመምሪያው የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ቡድን መሪ አቶ አማረ ጥበቡ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
ለ318 ተጨማሪ ነጋዴዎች የጽሁፍ ማሰጠንቀቂያ መሠጠቱን የጠቆሙት አቶ አማረ÷ 9 የመኝታ አገልግሎት ተቋማት ተከሰው ጉዳያቸው በህግ እየታየ ነው ብለዋል።
መምሪያው ባደረገው ቅኝት ሸቀጦችን መከዘን፣ ጊዜያቸው ያለፈባቸው እቃዎችን ለገበያ ማቅረብ እንዱሁም ዋጋ ጨምሮ መሸጥን ተመልክቻለሁ ያለ ሲሆን እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አሳውቋል፡፡
ወቅቱ የመረዳዳትና ተጋግዞ የማለፍ መሆን አለበት ያሉት አቶ አማረ÷ ማህበረሰቡ ህገ ወጥ ሂደቶችን ሲመለከት በጥቆማ ሊተባበር ይገባል ብለዋል።
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!