የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ የስራ ርክክብ አደረጉ
አዲስ አባባ፣ መስከረም 28፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በአዲሱ የመንግስት ምስረታ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ አደም ፋራህ ከቀድሞው የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡
አቶ ብናልፍ አንዷለምን ጨምሮ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ከፍተኛ አመራሮች በዛሬው እለት ከብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች እንዲሁም ወደፊት የታቀዱ እቅዶች ላይ ገለፃ ተደርጓል፡፡
አቶ አደም ፋራህ የጽህፈት ቤቱ ሰራተኞችን ተዟዙረው በመጎብኘት ማበረታታትቸውን ከብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!