ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣መስከረም 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የዋናው መ/ቤትና ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ፡፡
የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ አልምፀሃይ ጳውሎስ እና የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልጋሎ ድጋፉን አስረክበዋል፡፡
ኤጀንሲዉ መከላከያ ሰራዊቱ ባለበት ሁሉ መድኃኒትም ሆነ የህክምና ግብዓት እያቀረበ እንደሚገኝ የገለጹት ዳይሬክተሩ÷ ለመከላከያ ድጋፍ ማድረጋችን ሀላፊነታችንም ግዴታችንም ጭምር ነው ብለዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ብርጋዴል ጀኔራል አስረስ አያሌው÷ለሀገርም ሆነ ለመከላከያ ኤጀንሲው እያደረገ ያለውን የህክምና ግብዓት በማቅረብ አስተዋፅኦዉ ቀላል አይደለም ብለዋል፡፡
ድጋፉ ትልቅ ትርጉም ያለው እንደሆነና በሞራልም በግባቶችም የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መግለፃቸውን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!