አዲሱ ምዕራፍ የራሳችንን ጉዳይ በራሳችን እንደምንፈጽም ያሳየ ነው- ዶክተር ሄኖክ ስዩም
አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የተጀመረው አዲስ ምዕራፍ የራሳችንን ጉዳይ በራሳችን እንደምንፈጽም ያሳየ ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ዶክተር ሄኖክ ስዩም ገለጹ።
አዲሱ ምዕራፍ ጉዳዮቻችንን በራሳችን አቅም መከወን እንደምንችል የታየበት ነው ያሉት ዶክተር ሔኖክ፥ በሁሉም መስክከውጭ አገራት ጫና ለመላቀቅና ራሳችንን ለመቻል ጠንክረን የምንሰራበትም ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያውያን አቅማችንን በማሳደግ ሰላማችንን ማረጋገጥ፣ የምግብ ወስትናችንን ማረጋገጥ፥ ለዚህም በሁሉም መስክጠንክረን መስራት ይኖርብናል ነው ያሉት።
በዚህ አዲስ ምዕራፍ ኢትዮጵያዊያን የራሳችንን መንግስት በራሳችን የምንመርጥ፣ የራሳችንን ጉዳይ ራሳችን የምንፈታ ሉዓላዊ ሕዝብ መሆናችንን አሳይተናል ማለታቸውንም የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።
ሉዓላዊነታችንን ለማንም አሳልፈን የማንሰጥ ነን፤ ይህን ጥሶ ለሚመጣ ደግሞ የእጁን አግኝቶ እንደሚመለስ ታሪክ ምስክር ነው ሲሉ ጠቅሰዋል።
በቀጣይም ከድህነት ለመውጣትና ሉዓላዊነታችንን ሙሉ ለማድረግ ጠንክረን መስራት ያስፈጋል ብለዋል።
“ኢትዮጵያ ሉዓላዊ መንግስት ያላት ሉዓላዊት አገር ናት” ያሉት ዶክተር ሔኖክ ይህ ሕዝብና መንግስት ሁሉንም በራሱ
የማድረግ ሙሉ አቅም አለው ብለዋል።
የአሜሪካ መንግስትና ተባባሪዎቹ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በመዳፈር ጫና የማድረግና እጅ የመጠምዘዝ ሙከራ ተቀባይነት እንደሌለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳየቱንም ተናግረዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!