ጀግኖቻችን በሠላም እንድንማር የከፈላችሁትን መስዋዕትነት አንዘነጋም- የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኙት ለመከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ 16 የእርድ ሰንጋዎች ድጋፍ አድርገዋል።
ውድ ጀግኖቻችን እኛ የደብረ ታቦር ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች በሠላም እንማር ዘንድ እየከፈላችሁት ያለውን የህይወት መስዕዋትነት መቼም አንረሳውም በሚል መሪ ቃል ነው ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ 16 ሠንጋዎችን የለገሱት።
የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፍቃደኝነት መንግስት ከመደበልን የምግብ ሬሽን በመቀናነስ በድንበር ላይ ሆኖ የእኛን ደህንነት ለሚጠብቅልን ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊት እና ለሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ድጋፍ አድርገናል ብለዋል፡፡
ይህ ድጋፍም አሸባሪው ህውሓት እስኪደመሰስ አጠናክረን እንቀጥላለን ነው ያሉት፡፡
ድጋፉን የተረከቡት በግንባሩ የሚገኝ አሀድ ስንቅ ዕደላ ሃላፊ ኮ/ል ሽመልስ ብርሀኑ፣ ከራሳችሁ ሬሽን ቀንሳችሁ ላደረጋችሁት ድጋፍ ምስጋና ይገባችኋል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!