Fana: At a Speed of Life!

በዞኑ በመኸር እርሻ ልማት ከ7 ሚሊየን ኩንታል በላይ ለመሰብሰብ እየተሠራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉራጌ ዞን በመኸር እርሻ ልማት ከ142 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም እርሻ የለማ ሲሆን በዚህም ከ7 ሚለየን 641 ሺህ በላይ ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል ገለጹ፡፡
ይህ እቀድ የተያዘው መሬት ፆም ማደር የለበትም በሚለው ሀገራዊ የንቅናቄ መርሀ ግብር በተሰራው ስራ ነው መሆኑን አቶ መሀመድ ተናግረዋል፡፡
ዘንድሮ በኩታ ገጠም እርሻ ልማትና ሰፉፊ የመካናይዝ እርሻ ልማት ስራ ተግባራዊ በማድረግ 78 በመቶ የሚሆነውን የዞኑን የእርሻ መሬት ማረስ መቻሉን ጠቁመው÷ 142 ሺህ 700 ነጥብ 33 ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል ብለዋል።
በዚህም ዞኑ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር ከ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል በላይ ብልጫ ማግኘት የሣችላል ነው የተባለው፡፡
አርሶ አደሮች በበኩላቸው÷ የዘንድሮ መኸር እርሻ መንግስት በኩታ ገጠም እንድናመርት ክትትልና ድጋፍ በማድረጉ ብዙ ምርት የምናገኝበት ይሆናል ሲሉ ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት ገልፀዋል።
በመጪው እሁድም የፌደራልና የክልል የስራ ኃላፊዎች በዞኑ የተሰሩ የግብርና ስራዎችና የተገኙ ውጤቶችን ተዘዋውረው መስክ ምልከታ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በጎህ ንጉሱ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.